የኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ከ25 ሚሊየን በላይ ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ ይህን ያስታወቀው በዛሬው እለት መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡

ከተለያዩ የፍቃድ፡ የፍቃድ እድሳትና የብቃት ማረጋገጫ አገልግሎቶች ነው 25.3 ሚሊየን ብር መሰብሰብ የቻለው፡፡

የገቢ መሰብሰብ አፈፃፀሙ ከተያዘው እቅድ 134 ነጥብ 8 በመቶውን ያሳካ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለቴሌኮሙኒኬሽን የውስጥና የውጭ ኬብል ሥራ፣ ለማዞሪያ እና ለመሣሪያዎች ተከላ እና ጥገና ሥራ እንዲሁም የእሴት መጨመር አገልግሎትን ጨምሮ 302 ፈቃዶች የተሰጡ ሲሆን 258 ፈቃዶች ደግሞ ታድሰዋል።

28 የፍሪኩዌንሲ ፈቃዶች የተሰጡ ሲሆን፣ 46 የፍሪኩዌንሲ ፈቃዶች ደግሞ መታደሳቸውን ባለስልጣኑ ገልጿል።

ለ99 የሬዲዮ መገናኛ መሣሪያዎች እና ለ1 የቪሳት መሣሪያ የመጠቀሚያ ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን፣ የ4 የቪሳት መሣሪያዎች ፈቃድም ታድሷል ተብሏል።

ለ15 የፈጣን መልዕክት አገልግሎት ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን፣ የ5 የፈጣን መልዕክት አገልግሎት ፈቃድ መታደሱ በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *