የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሶስት ሰሚስተሮችን ትምህርት ብቻ እንደሚሸፍን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ሶስት ሲሚስተሮችን ብቻ ያካተተ መሆኑን ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ተግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት የ11ኛ ክፍል ሁለቱም ሲሚስተሮች እና የ12 ኛ ክፍል የመጀመሪያው ሲሚስቴር በፈተና አወጣጥ ሄደት ውስጥ የሚካተት ሲሆን በተመሳሳይ የ7ኛ ክፍል ሁለቱም ሲሚስተሮች እና የ8ኛ ክፍል የመጀመሪያው ሲሚስቴር ብቻ በ8ኛ ክፍል ፈተና ውስጥ የሚካተት ይሆናል።

ትምህርት ቤቶችም ያለፉትን ሶስት ሲሚስተሮች ዋና ዋና ነጥቦች ላይ የማካካሻ ትምህርት ለ45 ቀን እንደሚሰጡ ተነግሯል።

ክልላዊ እና ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችም ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ እና አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዛሬው እለትም በአዲስ አበባ የሚገኙ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርት ጀምረዋል፡፡

ያለፈው አመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተፈታኞችም ከጥቅምት 16 እስከ 30 2013ዓ.ም ምዝገባ እንደሚካሄድ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.