የቴአትር ቤቱ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ከፈለኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ህዳር መጀመሪያ ላይ የቴአትር ቤቱን 65ኛ አመት አስመልክቶ ለአገልግሎት ክፍት ልናደርግ ነበር ብለዋል፡፡
ነገር ግን ከጤና ጥበቃ ሚንስቴር መጥተው በጎበኙበት ወቅት ትያተር ቤቱ የጤና ሚኒስቴር ያስቀመጠውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ፕሮቶኮሎችን ባለማሟላቱ በቅርቡ እንዳይከፈት ማዘዛቸውን ተናግረዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ቴአትር ቤቱን ምቹ ለማድረግ በመጪው ረቡዕ ጽዳት እንደሚጀመር ሰምተናል፡፡
ቴአትር ቤቱ ስራ ሲጀምር 3 ቴአትሮች የተመረጡ ሲሆን 10 ያልበለጡ ተዋናዮች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡
በኮሮና ምክንያት ቴአትር ቤቱ በመዘጋቱ የቋሚ ተቀጣሪዎች ደሞዝ አልተቋረጠም ያሉት አቶ በፍቃዱ የተጋባዥ ተዋንያን ደሞዝ መቋረጡ እንዳሳሰባቸውም ተናግረዋል፡፡
ትያትር ቤቱ መች እንደሚከፈት በውል ያልታወቀው ሲሆን መስፈርቱን አሟልቶ ሲከፈት አዳራሹ ከሚችለው አንድ አራተኛው እንደተፈቀደለት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ ነግረውናል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም











