የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ግድያዎችን አወገዘ።

ኦነግ በተለይ ከለውጡ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ ድንገተኛ ጥቃቶች ግድያዎች እና ከባድ ዝርፊያዎች መበራከታቸውን አስታውቋል።

ይህ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የለውም ያለው ኦነግ፤መንግስት በቅድሚያ የዜጎችን የመኖር መብት እንዲከበር የማድረግ ግዴታ አለበት ብሏል።

የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ማንኛውም ዜጋ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን ሲገደል ጥቃቱ የሁላችንም እንደሆነ ሊሰማን ይገባል ብለዋል፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየደረሱ ያሉት ጥቃቶች መፈናቀሎችና ግድያዎችን ማውገዝ ለአንድ ወገን ብቻ የሚሰጥ ሳይሆን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር የሚንቀሳቀስ የትኛውም የፖለቲካ ፖርቲ ግዴታው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በማይታወቁ ሰዎች እና በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ስለሚገደሉት ዜጎቻችን ሁሌም ቢሆን እንሟገታለን የሚሉት አቶ ቀጀላ የዚህ ግድያ ሰለባዎች የመንግስት አመራሮች ጭምር በመሆናቸው ችግሩ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ መንግስት ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

መንግስት ጸጥታን በማስከበር ህብረተሰቡን ከስጋት ነጻ የሆነ ህይወት እንዲኖረው የማድረጎ ስራ ለዛሬና ለነገ የሚሰጠው ስራ እንዳሆነም ነው የሚናገሩት፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአባባ ሻምበል
ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *