ከሰሞኑ በኮንሶ ዞን፣ አማሮ፣ ዴራሼ፣ አሌና ቡርጂ ወረዳዎች ባሉ ግጭቶች የተጠረጠሩ 137 ሰዎች ተያዙ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ህዝቡ እርስ ችግር ባይኖርበትም ነባር ጥያቄዎችን ሰበብ በማድረግ እነዚህ የጥፋት ሀይሎች አማካኝነት በ17 ቀበሌዎች በተነሳ ግጭት የ66 ሰዎች ህይወት አልፏል። እንዲሁም በዚህ ግጭት ሳቢያም 39 ሰዎች የአካል ጎዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ130 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ ከሚኖሩበት ቀዬ ተፈናቅለዋል ብለዋል። በአካባቢው የህወሃትና ኦነግ ሸኔ […]

በአዲስ አበባ ከ107 ሺህ በላይ ሰዎች ኤች አይ ቪ ኤድስ በደማቸው እንዳለ ተገለፀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት በነገው እለት ቦሌ ለሚ ኢንደስትሪያል ፓርክ የሚከበረውን የአለም የኤድስ ቀን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። በአለም አቀፍ እና በሀገራችን በየአመቱ ህዳር 22 ቀን የሚከበረው የአለም የኤድስ ቀን ዘንድሮም የኤች አይ ቪን ለመግታት ፤ አለም አቀፋዊ ትብብር ፤ የጋራ ሀላፊነት በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገልጷል። በፅ/ቤቱ […]

በኢትዮጲያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ 113 ደም አፋሳሽ ግጭቶች መከሰታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ተናገሩ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ በመስጠት ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ አንስቶ 113 ደም አፋሳሽ ግጭቶች ተከስተዋል ብለዋል። በኦሮሚያ 37 ደም ያፋሰሱ ያፈናቀሉ እና ንብረት ያወደሙ ግጭቶች እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡ በአማራ 13 ደም ያፋሰሱ ግጭቶች እደነበሩ ጠቅሰው በተለይ በወልቃይት በቅንማንት ስም የተከሰተውን አንስተዋል፡፡ በቤኒሻንጉል እንዲሁም 15 የተከሰቱ ሲሆን በተለይ […]

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የካንሰር ጨረራ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ መሳሪያ ተተከለ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ሊኒየነር አክስሌሬተር የተባለ የካንሰር ጨረር ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ መሳሪያ በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለመጀመሪያ ጊዜ ተተክሏል፡፡ ወጪው ሙሉ በሙሉ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተሸፈነ ሲሆን የካንሰር የጨረራ ህክምና አገልግሎት የሚሰጠውም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መሆኑ ተነግሯል፡፡ የተተከሉት የህክምና መሳሪያዎች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተለያዩ ቦታዎች መሆኑም ተነግሯል፡፡ ይህ አገልግሎት በኢትዮጵያ መጀመሩም የካንሰር ህክምና አገልግሎትን ከፍ ለማድረግ የሚያስችል […]

የለውጥ ሃይሉን ተክትሎ የተፈጸሙ ችግሮችን በአስቸኳይ ለማስቆም የሚያስችል ስልጣን እና ዕድል እንዳልነበራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር አባላት ጋር ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ ከጥያቄዎቹ መካከልም እርሳቸው ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት ላይ ለምን ቀድመው የህወሃትን ጥፋት አላስቆሙም ነበር? አንዱ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩም “እኔ ራሴ በወቅቱ ዘመናዊ እስር ቤት ውስጥ ነበርኩ” ብለዋል በመልሳቸው፡፡ ሃገር እና ህዝብ የሚጠብቅብኝን ሃላፊነት መወጣት ለመቻል ቤተሰቦቼን ወደ ውጪ ሸኝቼ ለሁለት ወራት […]

ማደሪያ ያጣች እንስትን እኔ ጋር ታድሪያለሽ በሚል በማታለል ወደ ቤቱ በማስገባት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ18 ዓመት እስራት ተቀጣ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ወንጀሉ የተፈጸመባት እንስት ህይወቷ ማለፉም ተገልጿል። ተከሳሽ አብዱ መሐመድ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ክልል ልዩ ቦታው አሜሪካን ግቢ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ለጊዜው ማንነቷ ያልታወቀ ሟች ማደሪያ ችግሯት ከኔ ጋር ታድሪያለሽ በማለት ይዟት ከሄደ በኃላ ካልተያዙ አምስት የወንጀል ተካፋዮች ጋር በመሆን ሀይል በመጠቀም አስገድደው የመድፈር ወንጀል ሲፈጸሙባት በደረሰባት አካላዊ ጉዳት ምክንያት ህይወቷ ያለፈ በመሆኑ […]

የኢራን ቦምብ አባት በመባል የሚታወቁት ኢራናዊው ፋክህሪ ዛዴህ በቴህራን ተገደሉ።

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ኢራን የኑክሌር ሳይንስ ተመራማሪዋ በእስራኤል እንደተገደለባት ገልጻለች። ተመራማሪው ፋክህሪ ዛዴህ ትላንት በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን አቅራቢያ በመኪና በመጓዝ ላይ እያሉ ነበር በጥይት ተመተው ሂወታቸው ያለፈው ፡፡ የኢራን ከፍተኛ የኑክሌር ሳይንቲስት የሆኑት ሙህሰን ፋክህሪ ዛዴህ በረቀቀ መንገድ መገደላቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሀኒ በዚህ ግድያ እስራኤልን ከሰዋል፡፡ አንጋፋው የኢራን የኒውክለር ተመራማሪ ሙህሰን ፋክህሪ ዛዴህ […]

አዋሽ ባንክ 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር አመታዊ ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

አዋሽ ባንክ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 25ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው። ባንኩ በ2019/ 2020 አጠቃላይ የትርፍ መጠን የስንምት በመቶ ዕድገት በማሳየት 3.6 ቢሊየን አመታዊ ትርፍ ማግኘቱ ገልጿል ። ባንኩ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 57 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ብድር ማበደሩንም አስታውቋል። ባንኩ እንዳስታወቀው በ2019/ 2020 በጀት ዓመት የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 74 ነጥብ 3 ቢሊየን […]

ከ90 በላይ ዜጎቿ በዝሆኖች የተገደሉባት ኬንያ ጉዳዩ እንዳሳሰባት አስታወቀች።

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

የሀገሪቱ የዱር እንስሳት እንክብካቤ ቡድን እንዳስታወቀው በኬንያ የአምቦሴል ብሄራዊ ፓርክ በምስራቅ አፍሪካ ትልቁና በርካታ ዝሆኖች የሚገኙበት ፓርክ ሲሆን በሀገሪቷ ካሉት 34 ሺህ 800 ዝሆኖች ውስጥ ብዙዎቹ የሚገኙት በዚሁ ፓርክ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም የሰዎች ቁጥር መጨመር እና በፓርኩ ዙሪያ የሚደረገው ሰፈራ መስፋፋት ደግሞ ለሠዎችና ዝሆኖች ግጭት ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ አብዛኛዎቹ ሰዎች የሞቱት ደግሞ በዚሁ ፓርክ […]

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ የቆጣሪ ማንበቢያ ዘመናዊ መሳሪያ በስራ ላይ ማዋሉን አስታወቀ። ተቋሙ ከቆጣሪ ንባብ ጋር በተያያዘ የሚስተዋልበትን የአሠራር ክፍተት ለመፍታት የሚያስችል ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቆጣሪ ማንበቢያ መሣሪያ ስራ ላይ አውሏል፡፡ ተቋሙ በስራ ላይ ያዋለው የቆጣሪ ማንበቢያ መሳሪያ ኮመን ሜትር ሪዲንግ ኢንስትሩመንት /CMRI/ የተሰኘ በእጅ የሚያዝ ዘመናዊ መሳሪያ ሲሆን፤ የቆጣሪ አንባቢ በእያንዳንዱ የድህረ ክፍያ […]