በጉራ ፈርዳ አሁንም ታጣቂዎች ጥቃት ሊፈጽሙ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳለ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በጉራፈርዳ ባለፈው ጥቃት አደረሱ የተባሉት ታጣቂዎች ሙሉ ለሙሉ ባለመደምሰሳቸው አሁንም ስጋት እንዳለ የደቡብ ክልል የሰላምና የጸጥታ ቢሮ ገልጿል።

ከሁለት ሳምንት በፊት ለሊት ላይ ነዋሪዎች በመኖሪያ ቤታቸው ባሉበት በተፈጸመው ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት ማለፉ እና ከአምስት ሺ በላይ ዜጎች ደግሞ መፈናቀላቸው የሚታወስ ነው፡፡

ከዚህ ጥቃት በኃላ ምንም አይነት ችግር ባይኖርም ጥቃቱን አድርሰዋል የተባሉና የታጠቁ ሽፍቶች ሙሉ ለሙሉ ባለመደምሰሳቸው አሁንም ስጋት እንዳለ የደቡብ ክልል የሰላምና የጸጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ እና የግጭት መከላከል እና አፈታት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ጥቃቱ በተደራጀ ሁኔታ እንዲፈጸም ያደረጉ ተጠርጣሪዎችን የማደኑን ስራ የክልሉ ልዩ ሀይል ከመከላከያ ሰራዊት ጋር እየሰራ ነውም ብለዋል አቶ አንድነት፡፡

ይሁን እንጂ በአከባቢው ባለው ጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ እኚህ ያመለጡ ሽፍቶች በመሰወራቸው እነርሱን የመደምሰሱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው የሚያነሱት፡፡

እኚህ ሽፍቶች እስካልተደመሰሱ ድረስ ስጋቱ አሁንም እንዳለ መሆኑን አልሸሸጉም፡፡
ካለፈው ጥቃት ጋር በተያያዘ የአከባቢው ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ጨምሮ 84 ተጠርጣዎች መያዛቸውን አቶ አንድነት ነግረውናል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *