በጋምቤላ ከተማ ከ100 ሺህ ብር በላይ ሐሰተኛ የብር ኖት በግለሰብ እጅ ተያዘ፡፡

በጋምቤላ ከተማ ውስጥ አንድ ግለሰብ ግምቱ ከ 1 መቶ ሺ ብር በላይ የሆነን ሃሰተኛ የብር ኖት ወደ ባንክ በመውሰድ ለመቀየር ሲል እጅ ከፍንጅ መያዙን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የፀጥታ ዘርፍ ም/ል ሃላፊ አቶ ኦቶው ኦኮት ለኢትዮ ኤፍኤም እንዳሉት ግለሰቡ ከ 1 መቶ ሺ ብር በላይ ነባሩን የብር ኖት ሚመስለውን ፎርጅድ ብር በመያዝና ወደ አዲሱ የብር ኖት ለመቀየር ወደ ባንክ ባቀናበት ወቅት ነው በባንክ ሰራተኞች አማካኝነት በፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥጥር ስር ሊውል የቻለው፡፡

ግለሰቡ ላይ ተጨማሪ ማጣራቶች እየተደረጉበት መሆኑንም ሃላፊው ነግረውናል፡፡

በተጨማሪም በአካባቢውም ሆነ የከተማው ማህበረሰብ አዲሱን የብር ኖት ትክክለኛነት ብቻ ማጣራት ሳይሆን ነባሩ የብር ኖት አገልግሎቱ የሚያቃበት ጊዜ ይፋ እስከሚደረግ ድረስ ትክክለኛነቱን በሚገባ በማጣራት በሃሰተኛው የብር ኖት ከመታለል እንዲጠነቀቅ ሲሉ መልክታቸውን ነግረውናል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.