ከጉራ ፈርዳ ግጭት ጋር በተያያዘ ሶስት የዞን እና አስራ አንድ የወረዳ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ከሁለት ሳምታት በፊት ተፈጥሮ ከነበረው ግጭት ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች ከቀዬዓቸው ሲፈናቀሉ 31 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

ከዚህ ግጭት ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርሪዎች እንደተያዙ ተገልጿል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በግጭቱ ተሳትፎ የነበራቸው ሰዎች እየተያዙ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ስድስት የመንግስት ሰራተኞች እና ባለሙያዎች እንዲሁም አራት የፖሊስ አካላትም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ ፍቅሬ ተናግረዋል።

አንድ የቀበሌ አስተዳዳሪ እና ሶስት የቀበሌ ሰራተኞችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲሉ ተናግረዋል ዋና አስተዳዳሪው፡፡

ከጉራ ፈርዳ ግጭት ጋር በተያያዘም እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 87 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል።

የዞኑን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ የፖለቲካ እና የጸጥታ ስራዎች በተደራጀ መልኩ እየተሰራ እንደሆነ ዋና አስተዳዳሪው ነግረውናል።

ግጭቱ በተከሰተባቸው ሁለቱ ቀበሌዎች በድጋሚ ሌላ ችግር እንዳይከሰት ከኮማንድ ፖስቱ ጋር በመቀናጀት የጸጥታ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል አቶ ፍቅሬ፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *