የአማራ ባንክ ለዛሬ ጠርቶት የነበረውን መግለጫ ሰረዘ።

በምስረታ ላያ የሚገኘው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በቀጣይ እንቅስቃሴው ዙሪያ ዛሬ በአዲስ አበባ መግለጫ ለመስጠት መገናኛ ብዙሃንን ጠርቶ ነበር፡፡

በምስረታ ላይ ያለው አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ የሚጠይቀውን መስፈርት በሟሟላት አሁን በአክሲዮን ሽያጭ ላይ ነው የሚገኘው።

ባንኩ በምሥረታ ሂደት ላይ ሲሆን ከነሐሴ 11 ቀን 2011ዓ.ም አንስቶ በጀመረው የአክስዮን ሽያጭ እስካሁን ድርስ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ የአክሲዮን ሽያጭ መፈጸሙን አስታውቋል።

በጠቅላላው ከሸጠው አክስዮን ውስጥም ከ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ መከፈሉንም ገልጿል፡፡

ይህ ባንክ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ከሚያዝያ 8 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የአክሲዮን ሽያጩን ማራዘሙ ይታዎሳል፡፡

በባንኩ ቀጣይ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ለህዝብ መረጃ ለመስጠት ይዞት የነበረውን ፕሮግራም ከትናንት በስቲያ በኦሮሚያ ክልል በተፈጸመው ማንነት ላይ መሰረት ባደረገው ጥቃት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን ባንኩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በጅብሪል ሙሃመድ
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *