የአይሁድ ሰፋሪዎች ትራምፕ እንዲመረጡ እየፀለዩላቸው ነው።

የአይሁድ ሰፋሪ የሀይማኖት መሪዎች ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእምነታቸው መሰረት በመፅሐፍ ቅዱሳዊ መቃብር ስፍራዎች በሚደረግ ስነ ስርአት ወቅት እየጸለዩላቸው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ቦታው እስራኤል ከፍልስጤም ጋር የምትጋጭበት ዌስት ባንክ ነው ፡፡ ቦታው በትራምፕ አጋዥነት በእስራኤል በግድ የተወሰደ ነው፡፡

ትራምፕን ለመባረክ ነው የመጣነው ያሉ ሲሆን ላለፈው ልናመሰግናቸው የመጪውን ምርጫ ደግሞ እንዲያሸንፉ ልንፀልይላቸው ብለዋል የተቀደሰ ስፍራቸው ላይ በመስፈራቸው የተደሰቱት አይሁዶች፡፡

ዪሻይ ፍሌሸር የሄብሮን ሰፋሪዎች ቃል ቀባይ ሲሆን ጥንታዊና መፅሐፍ ቅዱሳዊ የመቃብር ስፍራዎች የመክፈት ስነ ስርአት እያከሄድን ነው ለትራምፕ የፀለይንለት ብለዋል፡፡

በስፍራው ከሚገኙ በአይሁድ፣ በክርስና እና በእስልምና እምነቶች የተቀደሱ ሰዎች ውስጥ አብርሀም ይገኝበታል ።

ዶናልድ ትራምፕ በአይሁዶችና በአረቦች መካከል አብሮ ተቻችሎ መኖርን ለማበረታታት በሚል የእስራኤል አረብ መቀራረብ ብለው በሰየሙትና የአብርሀም ስምምነት ተብሎ በተጠራው ድርድር እያሸማገሉ ይገኛሉ፡፡

ከ ጆ ባይደን ጋር ብርቱ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፉክክር የሚጠብቃቸው ትራምፕ በፍልስጤሞች ግን አይወደዱም፡፡ እየሩሳሌምን ለእስራኤል በመስጠት የአለም አቀፍ ህግን ሽረዋል ይሏቸዋል፡፡

በሔኖክ አስራት
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.