የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ከትናንት በስቲያ በኦሮሚያ ክልል ጉሊሶ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት በተፈጸመው ጥቃት ህይወታቸው ላለፉ እና ለተጎዱ ዜጎች ጥልቅ ሀዘናቸውን ገልፀዋል።
ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው በንጹሀን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት አውገዘዋል፡፡
ሊቀመንበሩ በመግለጫቸው አክለው እንደተናገሩት በጥቃቱ ምክንያት ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
እንደዚህ የመሳሰሉ ግጭቶችን ለመከላከል ጥልቅ የሆነ እና አካታች የሆነ ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ታናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ሰላምን ለማረጋገጥ በምታደርገው ጥረትም የአፍሪካ ህብረት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግም ነው ሊቀመንበሩ የተናገሩት፡፡
አካታች ውይይት በማድረግ ሰላም ለማስፈን መስራት እንደሚገባ አሳስበው ሕብረቱም ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም











