ማላዊ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዋቿ ሰጥታው የነበረውን ፈተና ሰረዘች፡፡

በማላዊ የሁለተኛ ደረጃ ፈተናዎች ተሰተው ካለቁ በኃላ ተሰርዘዋል ፣ በዚህም የተበሳጩ ተማሪዎች በብዙ የአገሪቱ ክፍሎች ወደ ጎዳና ወጥተው ተቃውሟቸውን አሰምተዋል ፡፡

መሰረዙ ከ 154 ሺህ በላይ ተማሪዎች የወደፊት ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ፡፡

የፈተናዎች ቦርድ ውሳኔውን የወሰደው የፈተና ወረቀቱቹ ተሰርቀው መሰራጨታቸውን ተከትሎ የፈተናው ታማኝነት ሊረጋገጥ ስላልቻለ ነው ብለዋል የትምህርት ሚኒስትሩ ፡፡

በመደበኛነት የማላዊ የሁለተኛ ደረጃ ፈተናዎች በሰኔ ወር የሚካሄዱ ቢሆንም በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት በድንገት ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተከትሉ ነበር የተላለፉት ፡፡

ተማሪዎች ፈተናቸውን የጀመሩት በጥቅምት 27 ሲሆን በህዳር አጋማሽ ያጠናቀቃሉ ፡፡

አሁን አዲስ ፈተና እንዲሰጥ ለመጋቢት ወር ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል ብሏል ቢቢሲ አፍሪቃ ፡፡

ከፈተናው ስርቁት ጋር በተያያዘ ወደ 40 የሚጠጉ ተማሪዎች ከአስተማሪ እና ነጋዴ ተጠርጥረው ተይዘዋል ፡፡

ፈተናዎቹ ከተሰረዙ በኋላ በነበረው አመፅ ሁለት ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ፡፡

በመዲናዋ ሊሎንግዌ የተቆጡ ተማሪዎች መንገዶችን በመዝጋት መኪናዎች ላይ በድንጋይ በመወረወራቸው የትራፊክ ፍሰት ተቋርጧል ፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *