በአፋር ክልል ጥቃቶችን ለመሰንዘር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 16 የታጠቁ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ክልሉ አስታወቀ።

የአፋር ክልሉ ሰላምና ደህንነት ሃላፊ አቶ ኢብራሂም ኡመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ከነ ትጥቃቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

እነዚህ የታጠቁ ሃይሎች በሰመራ-ሎጊያ መውጫ 6፣በአፋር እና ራያ በኩል ባለው ቦታዎች ላይ 8 እንዲሁም በአፋር ዞን አራት እና አንድ ላይ ሁለት በድምሩ 16 ታጣቂዎች ከነ ትጥቃቸው በአፋር የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሰር የዋሉት በአርብቶ አደሮች ጥቆማ እና እገዛ እንደሆነም ሃላፊው ነግረውናል።

“ተጠርጣሪዎቹ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ፣ከባድ መሳሪያ የታጠቁ እና ትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ናቸው” ያሉት ሃላፊው ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ መያዛቸውን ነግረውናል።

ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ ሌሊት ስድስት ሰዓት ላይ 6 አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪዎች ተከታትለው ወደ ትግራይ ለመሄድ ሲሞክሩ በጸጥታ ሃይሉ በቁጥጥር ስር ውለው ምን እንደጫኑ እና ማን እንዳሰማራቸው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም ሃላፊው ነግረውናል።

የአፋር አርብቶ አደሮች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በንቃት የክልሉን ደህንነት በመጠበቅ ላይ መሆናቸውንም አቶ ኢብራሂም ገልጸዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *