በኢትዮጵያ ካሉ የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ ተቋማት መካከል መስፈርቱን ያሟሉት 40 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከዘርፉ አመራሮች ከአሽከርካሪ ማሰልጠኛ እና ከተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማት ባለሀብቶች ጋር በአዲስ አበባ በመምከር ላይ ይገኛል።

ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ፣ኦሮሚያ፣አማራ እና ትግራይ ክልሎች በመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛዎች ጥራት ዙሪያ ያካሄደውን ጥናት ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በዚህ ጥናት መሰረትም በሀገር አቀፍ ደረጃ ካሉ 550 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ መስፈርቱን አሟልተው እየሰሩ ያሉት 40 በመቶዎቹ ያህሉ ብቻ ናቸው ተብሏል።

የተሽከርካሪ መመርመሪያ ማሽኖች ደረጃቸውን ያልጠበቁ ሆነው አገልግሎት የሚሰጡ እንዳሉ በጥናቱ ታውቋል።

የመብራት ሲስተም የሚሰራ ተሽከርካሪ ያላቸው የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት 63 በመቶዎቹ ብቻ ናቸውም ተብሏል።

ከ20 አመት በላይ በሆናቸው መኪኖች የሚያሰለጥኑ ተቋማትም እንዳሉ በግኝቱ ተረጋግጧል።

የአሽከርካሪ ምርመራ ተቋማትን በተመለከተ የምርመራ ቦታ በመስፈርቱ መሰረት ያሟሉ ቁጥራቸው አነስተኛ ሲሆን ይህም የሚያሳየው ህጋዊ ሳይሆኑ ፍቃድ እያገኙ ነው።

የማሽን እርማት (ካሊብሬሽን) የሚሰሩ አንድም የአሽከርካሪ ምርመራ ተቋማት የሉም ሲሉም ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.