የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ ኤ 350 ባጋጠመው የሃይድሮሊክ ችግር ምክንያት በህንዷ ሞምባይ ከተማ ለማረፍ መገደዱን ከአቪሽን ጋር የተገናኘ ዜናዎችን የሚያወጣው ሲንፕል ፍላይንግ ዘግቧል፡፡
አውሮፕላኑ ከሪያድ ወደ ህንዷ ባንጋሎር ከተማ እቃ ጭኖ በመጓዝ ላይ ሳለ የሃይድሮሊክ ፍሳሽ ስላጋጠመው መሆኑ ዘገባው ጠቁሟል።
አውሮፕላኑ አቅጣጫውን የቀየረው ለሁለት ሰአት ተኩል ያህል ከበረረ በኃላ መሆኑም ተነግሯል፡፡
አውሮፕላኑ 8 ሰራተኞችን የጫነ ሲሆን የጭነት አገልግሉት የሚሰጥ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
በአሁን ጊዜ ይህ እክል የገጠመው አውሮፕላን በዚችው ሞምባይ አየር ማረፊያ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም











