ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ ላለማጓጓዝ የወሰነውን ውሳኔ ማሰረዙን የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር አስታወቀ።

ማህበሩ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባካሄደው ስብሰባ መንግስት እስከ ዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የትራንስፖርት ታሪፍ የማይሻሻል ከሆነ ተሽከርካሪዎቻችንን እናቆማለን ብለሎ ነበር።

ነገር ግን አሁን ባለው የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታና ከመንግስት አካላት ጋር ባደረግነው ስምምነት እስከ ጥቅምት 30 አስቀምጠነው የነበረውን ውሳኔ አንስተናል ሲሉ የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጸጋ አሳመረ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን በኪሳራ ውስጥ ብንሆንም አገር የባሰ ጉዳት እንዳይደርስባት ስንል ስራችንን ለመቀጠል ፈቅደናል ብለዋል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *