እስራኤል የአንበጣ መንጋ ተከላካይ ግብረ ሀይሏን ወደ ኢትዮጵያ ላከች።

የበረሀ አንበጣን ለመከላከል የሚያግዝ ግብረ ሀይል እስራኤል ወደ ኢትዮጵያ መላኳን በኢትዮጵያ የእስራኤል ኢምባሲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከጥቂት ወራት ጀምሮ ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የአንበጣ መንጋን እየተጋፈጠች እንደሆነ ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋቢ አሽካንዚ ግብረ ሀይሉ እንዲመጣ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

የእስራኤል ኤምባሲም ተልዕኮውን በመምራት ከኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይሰራል።

ግብረ ሀይሉ 2 ቶን የሚመዝን የአንበጣ መከላከያ መሳሪያ ያመጣ ሲሆን በ2 ሳምንት ውስጥም ስራውን ለማጠናቀቅ አቅዷል።

ከ200 በላይ የአንበጣ መከላከያ ላይ የሚሰሩ ሀገር በቀል ተቋማትም ስልጠና እንደሚሰጣቸው ታውቋል።

ይሄ ተልዕኮ የሁለቱን ሀገራት ረዘም ያለ መልካም ግንኙነት ያሳያልም ተብሏል

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.