የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት አማዱ ቶማኒ ቱሬ በ72 ዓመታቸው አረፉ ፡፡

አማዱ ቶማኒ በህክምና ላይ በነበሩበት በቱርክ ዛሬ ረፋድ ላይ ነው ያረፉት ፡፡

ከቀናት በፊት ነበር ወደ ቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል ለህክምና ያቀኑት ፡፡

ከማሊ ከመነሳታቸው በፊት በዋና ከተማዋ ባማኮ ድንገተኛ የልብ ቀዶ ጥገና ተደርጓላቸው እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል

እ.ኤ.አ በ2002 ጄኔራል አማዱ ሀያ ሳኖጎ በሚመራው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እስከተወገዱበት ጊዜ ድረስ የማሊ ፕሬዚዳንት ነበሩ ፡፡

ቱሬ እ.ኤ.አ. በ 1992 ምርጫ ኮሚሽን ካደራጁ በኋላ ለአመታት ዘለቀውን የወታደራዊ አገዛዝ እንዲያበቃ በማድረግ እና ስልጣናቸውን ለዜጎች አሳልፈው መስጠታቸው ምስጉን አድርጓቸዋል፡፡

“የዴሞክራሲ ወታደር” የሚል ቅጽል ስም በአገሬው ህዝብ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *