የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ፑቲ አብዛኛው የሶሪያ ግዛት በአሁኑ ወቅት አንጻራዊ ሰላም በመኖሩ በሚሊየን የሚቆጠሩት ሶሪያዊያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው በመመለስ ሶሪያን መልሶው መገንባት አለባችሁ ብለዋል ።
የሶሪያን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉ ታዛቢዎች ግን በሀገሩቱ ያለው ፣ በተላይም በምዕራብ በኩል ያለው ጦርነት ብዙሃን ስደተኞችን ለመመለስ አሁን ጊዜው አይደለም ብለዋል ።
ሩሲያ ለሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ በምታደርገውን የጦር ድጋፍ ለሀገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት እና ለንጹሐን ግድያ ትልቅ ድርሻ ያላት በመሆኗ በተደጋጋሚ ትችት እንደሚቀርብባትም ተነግሯል ።
ከበሽር አላሳድ ጋር በ video call በአካሄዱት ውይይት ፑቲን ደማስኮ ዜጎቿን ለመቀበል ከነገ ጀምሮ እቅድ ትያዝ ብለዋል ።
አልጄዚራ እንደዘገበው ፣ ሞስኮ የሶሪያ ስደተኞችን ያለፍላጎትታቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ መወሰኗን ፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ከአሜሪካ ባለስልጣናት ወቀሳ ተሰንዝሮባታል ።
አለም አቀፍ ሽብርተኝነት በእጅጉ መቀነስ ስለተቻለ ዜጎች ወደ ሀገራቸው በመመለስ እና በሂደት መደበኛ ኑሮ መጀመር እንዳለባቸው ፑቲን ተናግረዋል ።
በሶሪያ በ 9 አመታት ውስጥ በተካሄደ የእርስ በእርስ ጦርነት 500 ሺህ ዜጎች ተገድለዋል ፣ 5 ነጥብ 6 ዜጎች ሚሊየን ዜጎች ደግሞ ሀገራቸውን ለቀው ተሰደዋል እንዲሁም በጦርነቱ 6 ሚሊየን ዜጎችን የሀገር ውስጥ ስደተኛ አድርጓቸዋል ተብሏል ።
በዳንኤል መላኩ
ሕዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም











