መንግስት ከህወሀት ቡድን የቀረበለትን የእንደራደር ጥያቄ እንዳይቀበል የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት የድጋፍ እና የልማት ማህበር አሳሰበ።

መንግስት ስሞኑን በጥፋት ሀይሎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ አቅዶበት የገባበት እንዳልሆነ ማህበሩ ተናግሯል።

የማህበሩ ፕሬዘዳንት ሀምሳ አለቃ ብርሃኑ አማረ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በአሳፋሪው የህወሃት ጁንታ ላይ የተጀመረው አገርን የማዳን ስራ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

ከጦርነቱ ጎን ለጎንም ንፁሀን ዜጎችን ከሞት የማዳን ስራው መቀጠል አለበትም ብለዋል።

ሀምሳ አለቃ ብርሀኑ እንደሚሉት ይኸው ቡድን አሳፋሪና አስነዋሪ ድርጊቶችን ሲፈጽም የኖረ በመሆኑ ቡድኑ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተወግዶ ትውልድ እና ሀገር ማረፍ አለባቸው ብለዋል።

አሳፋሪው የህወሀት ቡድን ያቀረበውን የእንደራደር ጥያቄም መንግስት በፍጹም መቀበል እንደሌለበትም አሳስበዋል።

ይልቁንም መንግስት ቡድኑ የሚጠፋበትን እርምጃ በሙሉ አቅሙ እንዲቀጥልበትም ጠይቀዋል።

በተለይ ደግሞ የዚህ ቡድን ሁሉም እንቅስቃሴዎች ለትግራይ ህዝብ ትልቅ ስቃይ በመሆኑ ከዚህ በኋላ ይህ ህዝብ ማረፍ አለበት ብለዋል።

ስለሆነም ሰላማዊ ዜጎች በሰላም እንዲንቀሳቀሱ፣ በሰላም ዉለው በሰላም እንዲገቡ በአጠቃላይ ሀገራችን በአንድነትና በፍቅር እንድትቀጥል ሲባል መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እስከመጨረሻው ድረስ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

የማህበሩ አባላት የተጀመረው አገርን የመታደግ ዘመቻን በቻለው መጠን ሁሉ ይደግፋል ያሉት ፕሬዘዳንቱ በትግራይ ክልል ያሉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት በህወሃት ላይ የተጀመረውን እርምጃ እንዲደግፉም ማህበሩ ጥሪውን አስተላልፏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በጅብሪል ሙሀመድ
ሕዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.