በአሶሳ ከተማ ዛሬ ረፋድ ለሽብር ስራ ሊውል ይችላል በሚል ተጠርጥሮ በፖሊስ የተያዘው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ቆጠራው እስካሁን አልተጠናቀቀም።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱላዚዝ ሙሀመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የህወሀት ቡድን ተላላኪዎች በክልሉ ከፍተኛ የጥፋት ሴራ ደግሰው ቢንቀሳቀሱም አስቀድመን እርምጃ በመውሰዳችን የታሰበውን ሴራ አክሽፈናል ብለዋል፡፡

በክልሉም የተለያዩ ከተሞች የሽብር ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ግለሰቦች ዛሬ ረፋድ በአሶሳ ከተማ በሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ መያዙ የተገለጸ ሲሆን ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን ለማወቅ ቆጠራ ላይ መሆናቸውንም ኮሚሽነር አብዱልአዚዝ ነግረውናል።

ይህ ገንዘብ ከመቀሌ መላኩን የተናገሩት ኮሚሽነሩ የህወሃት ቡድን በውጊያ ላይ ሆኖም ሽብር ከመፍጠር ወደ ኋላ እንደማይል ማሳያ ነውም ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በህግ ጥላ ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ለሽብር ተልዕኳቸው ማስፈጸሚያ በሚል ወደ አሶሳ የተላከው እና በፖሊስ እጅ የሚገኘውን የገንዘብ መጠን ለማወቅ ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ ቆጠራ ላይ ነን ቆጠራው ሰልችቶናል ብለውናል።

እስካሁን ባለን ቆጠራ እና ግምት የተያዘው ገንዘብ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ሊሆን እንደሚችል እና ቆጠራው እንዳለቀ መረጃውን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን ሲሉም ነግረውናል።

በደረሰ አማረ
ሕዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *