በፓኪስታን የሚገኝው የአሜሪካ ኤምባሲ ይቅርታ ጠየቀ፡፡

ኤምባሲው ይቅርታ የጠየቀው በቲውተር አካውንቱ ላይ በለጠፈው ወሬ ነው፡፡
በኤምባሲው የቲውተር አካውንት ላይ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን ዘመናቸው ሊያበቃ ተቃርቧል የሚል መልእክት መለጠፉ ተከትሎ ነው ይቅርታ ሊጠይቅ የቻለው፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸው የሚያስረክቡ ከሆነ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸው ሊያበቃ ይችላል ሲል ነበር በቲውተር አካውቱ ላይ ለጥፎ የተገኘው፡፡

ይህንንም ተከትሎ ኤምባሲው ከሀገሪቱ ባለስልጣነት ከፍተኛ ትችት ከደረሰበት በኃላ ነው ይቅርታ የጠየቀው፡፡

የፓኪስታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በታሪክ ታይቶ የማይተወቅ አሳዛኝ ክስተት ሲሉ የኤምባሲው ድርጊት ያወገዙት፡፡

ይህ ሆን ተብሎ የተሰራ ስራ ነው ድርጊቱ የሁለቱን ሀጋራት ግኑኝት የሚያጠለሽ ነው ማለታቸውን የሩስያው የዜና ወኪል አርቲ ዘግቧል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሕዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *