ፈረንሳይ በማሊ አንድ ከፍተኛ የአልቃይዳ መሪ መግደሏን አስታወቀች፡፡

የፈረንሳይ መከላከያ ሚንስትር ፍሎረንስ ፓርሊ ከደቂቃዎች በፊት በሰጡት መግለጫ በሰሜን ምስራቅ ማሊ በተካሄደ ዘመቻ በሰሜን አፍሪካ የአልቃይዳ ክንፍ ወታደራዊ መሪ ባህ አግ ሙሳ በሀገሪቱ ወታደሮች መገደላቸውን አስታውቀዋል፡፡

እኚህ የጂሃዳዊ እንቅስቃሴ መሪ በማሊ እና በዓለም አቀፍ ኃይሎች ላይ ለተፈጸሙ በርካታ ጥቃቶች ተጠያቂ ናቸው ተብሎ ይታሰባል፡፡

መከላከያ ሚንስትሯ ፓርሊ በሰጡት መግለጫ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ይህ ትልቅ ስኬት መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በሰሜን አፍሪካ የአልቃይዳ ክንፍ ወታደራዊ መሪ ሙሳ በአሜሪካ የሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ ከተቀሱ ሽብርተኞች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡

ፈረንሣይ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አማፅያንን ለመዋጋት ከ 5 ሺህ በላይ ወታደሮችን አሰማርታለች፡፡

እነዚህም ወታደሮች በማሊ ከፍተኛ እንቅስቃሴዎችን በማክሸፍ ሲሳተፉ ቆይተዋል፡፡

የፈረንሳይ ወታደሮች በዚህ ወር ብቻ በማዕከላዊ ማሊ ከ 50 በላይ ጂሃዲስተኞችን መግደላቸውን ዘ ዲፌንስ ፖስት ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.