በኦሮሚያ ክልል ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለጸ።

በምዕብ ሀረግጌ ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ በፍጥነት ማሽከርከር ምክንያት የ1 ሰው ህይወት ሲያጠፋ በሰሜን ሸዋ ወረጃርሶ ወረዳ ፒክ አፕ ተሸከርካሪ ለእግረኛ ቅድሚያ ባለመስጠት የ6 አመት ህፃንን ህይወት ቀጥፏል ሲሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ ሪፖርትና ጥናት ግንባታ ዲቪዥን ባለሙያ ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በቢሾፍቱ ከተማ ደግሞ ባጃጅና ሚኒባስ ታክሲ ተጋጭተው 2 ከባድ አደጋ የደረሰ ሲሆን መንስኤውም የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑን ሰምተናል።

ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰንዳፋ በኬ ከተማ ቀበሌ 02 ባጃጅና የቤት አውቶሞቢል ተጋጭተው እንዲሁ ከባድ አደጋ ደርሷል።

ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ ሌላው በከባድ አደጋ የተመዘገበው ደግሞ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ኮልቦ ከተማ ቀበሌ 01 ባጃጅና ፓትሮል ተጋጭተው 3 ሰው ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።

በነዚህ አደጋዎች ምክንያትም 980 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ ተናግረዋል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *