በጋምቤላ ከልል ዲማ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያና አንድ F1 የእጅ ቦንብ ከስድስት ተጠርጣሪ ጋር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የጦር መሳሪያው ሰሞኑን ከደቡብ ሱዳን ድንበር ወደ ዲማ ወረዳ በማስገባት ሊሸጥ ሲል ነው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ፈጥኖ ዋና ሳጂን ጋዲሳ ቶሎሳ እንዳሉት በወረዳው በተለያዩ ጊዜያት ህገወጥ የጦር መሳሪያ እንደሚያዝ አስታውሰው በዚህ ድርጊት የሚሳተፉ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሰሞኑን በቁጥጥር ስር የዋለው የጦር መሳሪያ ከደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ ወደ ዲማ ሊገባ ሲል በህብረተሰብ ጥቆማ መያዙን አስታውቀዋል፡፡

የክልሉንና የሃገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ አካላት አላማቸውን ለማሳካት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሊያካሂዱ ስለሚችሉ ሁሉም አካባቢውን ነቅቶ መጠበቅ እንደሚኖርበት አመልክተዋል፡፡

ለዚህም ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጎን ቆሞ የሚያደርገው የመረጃ ልውውጥ አበረታች መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ህገወጦችን ለማስቆም በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ጥቆማውን እንዲቀጥል የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት አሳስቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ትኩስ ዜናዎችን፣ ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሕዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *