የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ከኮቪድ 19 ስጋት ጋር ተያይዞ ራሳቸዉን አገለሉ።

ቦሪስ ጆንሰን ራሳቸዉን ያገለሉት Lee ሊ አንደርሰን ከተባሉ የሀገሪቱ የፓርላማ አባል ጋር ለ30 ደቂቃ ያህል ዉይይት ካደረጉ በኋላ አንደርሰን ፖዚቲቭ ሆነዉ በመገኘታቸዉ ነዉ ተብሏል፡፡

ይሁንና ቦሪስ ጆንሰን እስካሁን ምንም አይነት የቫይረሱን ምልክት አለማሳየታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከዚህ ቀደም በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዉ ጽኑ ህሙማን ክፍል ሳይቀር ገብተዉ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በተያያዘ ዜና በእንግሊዝ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ በስፋት መስጠት ተጀምሯል፡፡

ጃንሰን በተባለዉ የቤልጀም ኩባንያ የተሰራዉ ይህ ክትባት፣ የጉንፋን አምጭ ተህዋሲያንን የዘረ-መል ማሻሻያ በማድረግ የኮቪድ 19 ተህዋሲን እንዲዋጋ ተደርጎ የተዘጋጀ ነዉ፡፡

በእንግሊዝ ለኮቪድ 19 ክትባት ከተሞከሩት ዉስጥም ይህ 3ኛዉ ነዉ፡፡

እንግሊዝ አሁን ወደ ሙከራ ያስገባችዉ ክትባት በ 6 ሽህ ሰዎች ላይ ነዉ የሚመከረዉ፡፡ዉጤቱን ለማወቅም በትንሹ ከ6 እስከ 9 ወራትን ሊወስድ ይችላል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሩሲያ ሰራሹ የኮቪድ 19 ክትባት እስከ 90 በመቶ ድረስ አስተማማኝ ነዉ ማለቷን ተከትሎ ሀገራት ቀድሞ ለመገኘት በእጃቸዉ ያሉትን የምርምር ዉጤቶች ሙከራ ላይ እያዋሏቸዉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ትኩስ ዜናዎችን፣ ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ሕዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *