ሞደሬና የተባለው ፋብሪካ የኮሮና ቫይረስን 95 ከመቶ የሚፈውስ እና የሚከላከል ክትባት ማግኝቱን ሮይተረስ ከደቂቃዎች በፊት በሰበር ዜናው አስነብቧል፡፡
ክትባቱ በ30 ሺህ ያህል ሰዎች ላይ ተሞክሮም አመርቂ ውጤት ማምጣቱን ነው የተነገረው፡፡
ሞደሬና የተባለው የመድሀኒት አምራች ፋብሪካ ሰሞኑን ፒፍዘር ከተባለው የመድሀኒት አምራች ፋብሪካ ጋር በመተባበር በርካታ ቁጥር ያለው ክትባት ለሀገራት ሊያቀርብ እንደሆነም አስታውቋል፡፡
አሁን የተገኝው ከትባት የመጨረሻ የሙከራ ደረጃ ሙሉ በሙሉ ማለፉንና ውጤታማ መሆኑን የገለጸው የህ ፋብሪካ እስከ ፈረንጆቹ አዲስ አመት ድረስ 60 ሚሊየን ብልቃጥ ክትባት አቀርባለሁ ብሏል።
በሚቀጥለው አመት የአሜሪካ መንግስት አንድ ቢሊየን ክትባት ለመግዛትም ማዘዙን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
አሜሪካ አሁን ላይ ውጤታማ ናቸው የተባሉ ሁለት ክትባባቶችን ለአለም አስተዋውቃለች፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሕዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም











