በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ህግን የማስከበር ሂደት ወንጀለኞችን ለህግ ከማቅረብ ያለፈ አላማ እንደሌለው ተገለጸ።

የጠቅላይ ሚንስቴር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ሕወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መለየት የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እና ሕገ ወጥ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሜ ያረጋግጣል::

ነገር ግን ይህ ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ በብሔር ወይም በሌላ ወገንተኝነት ላይ የተቃኘ ነው የሚለውን የተሳሳተ እሳቤ አጥብቆ ያወግዛል፡፡

በአሁኑ ወቅት በትግራይ የሚካሄደው ሕግ የማስከበር ሥራ በዋነኝነት ኢትዮጵያን በማተራመስ ላይ በተሠማሩ ሥርዓት አልበኞች፣ በተንኮልና በሤራ በተሞሉ የሕወሐት ቡድን አባላት ላይ ያነጣጠረ ስለመሆኑ ማንም ሰው ጥርጣሬ ሊገባው አይገባም፡፡

በትግራይ ክልል ሕዝብ ላይ ሳይቀር የከፋ በደል የሚፈጽመውን ይህን የሕወሐት ጁንታየወንጀል ሰንሰለት ለማስቆም የፌዴራሉ መንግሥት ቆርጦ ተነሥቷል፡፡

በዚህ ሕግ የማስከበር ዘመቻ የትግራይ ሕዝብ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ይሆናል፡፡

ለኢትዮጵያ ያለን ራእይ በብዝኃነት የሚኮሩ ብሔር ብሔረሰቦች በአንድነት የሚኖሩባት የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ ሕዝባችን ነው።

በዚህ ሕዝባችን ላይ ምንም ዓይነት ክፉ ነገር እንዲደርስ አንፈልግም። ይሄንን የሚያደርጉትንም አንታገሥም ሲል ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
ሕዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *