በደቡብ ክልል ሰገን ህዝቦች ዞን በአሌ እና በኮንሶ በተነሳው ግጭት ብዙዎች መሞታቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ።

ካለፈው አርብ እለት ጀምሮ በደቡብ ክልል በአሊ አካባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት ለቀናት መዝለቁ ነው የተሰማው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአካባቢው ነዋረዎች እንደሰማው አብዛኛው ነዋሪዎችና የመንግስት ሰራተኛ በሳውላ በኩል መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው መሰደዳቸውን ሰምተናል፡፡

ከዚህ ጥቃት በተአምር ነው የተረፍኩት ያለችን አንድ የአካባቢው ነዋሪ “እንዲህ አይነት ችግሮች በአካባቢው ላይ ከወረዳና ከዞን ጥያቄ ጋር በተገናኘ የተለመደ እየሆነ ቢመጣም አሁን ግን ጥቃትና ግድያውን ፈጸመዋል የሚባሉት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” ስትል ግምቷን ተናግራለች፡፡

በአርባ ምንጭ ባለው የነጭ ሳር ፖርክ አቅራቢያ ባለው የአባያ ሀይቅ አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ምሽግ እንዳላቸው እና ከዚህ ፓርክ እየወጡ እያጠቋቸው እንደሆኑ ተፈናቃዮቹ ነግረውናል፡፡

ከቅርብ ቀናት በፊትም መንግስት ባደረገው መጠነ ሰፊ ዘመቻ የጦር መሳሪዎች መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

እኛም ቢሆን በአካባቢያችን ላይ የምናያቸውን ፀጉረ ልውጥ ሰዎችን ለአካባቢው ፖሊስ ጠቁመናል ነው ያሉት፡፡

ይሁን አንጂ አሁን ላይ ጥቃቱን በሚያደርሱት ታጣቂዎች ላይ የጸጥታ ሀይሉ እርምጃ እየወሰደ አለመሆኑንም ነግረውናል፡፡

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ምላሽ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው አንድ የደቡብ ክልል መንግስት ስማቸውና ድምጻቸው እንዳይገለጽ ጠይቀው በተጠቀሱት አካባቢዎች ጥቃት መፈጸሙን ተናግረዋል።

በዚህ ጥቃት ምክንያትም ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ዜጎች በዚህ ጥቃት ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን እና ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ነግረውናል።

ከትላንት ጅምሮም የደቡብ ክልል መንግስት የጸጥታ ተቋማት አመራሮች ወደ ቦታው አምርተው በቀጣይ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች በመምከር ላይ መሆናቸውንም ሃላፊው ገልጸዋል።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *