የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው በሚኒስቴሩ አራት ወራት የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።
ከሀገር ውስጥ ታክስ ለመሰብሰብ የታቀደው 67.6 ቢሊየን ብር ሲሆን ከ75 ቢሊየን በላይ ብር ተሰብስቧል ብለዋል።
ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 36.9 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 36.4 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል።
ከሎተሪ ሽያጭ 24.2 ሚሊየን ለመሰብሰብ ታቅዶ 83.7 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል።
በአጠቃላይ በ2013 በጀት ዓመት 290 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን በ4 ወር ብቻ 107 ቢሊየን ብር መሰብሰብ ተችሏል።
ይህም በ2012 ከተሰበሰበው የ19.1 በመቶ እድገት አሳይቷል።
በደረሰ አማረ
ህዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም











