በኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት 8 ሰዎች በአንበሳ መበላታቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 8 ሰዎች በአንበሳ ተበልተው ህይወታቸው አልፏል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ 3 ሰዎች በጋምቤላ ብሄራዊ ፓርክ አቦቦ ወረዳ 5 ሰዎች በአንበሳ መበላታቸውን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ወረዳ 44 ፍየሎች በአንበሶች መበላታቸው ተገልጿል።

በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ በሰውና ጅብ መካከልም በተደጋጋሚ ግጭት እንደሚፈጠር የተገለጸ ሲሆን ዋናው የሰዉና የዱር እንስሳቱ ግጭት መንስኤ ሰዎች በዱር እንስሳቱ መኖሪያ በመግብታቸው ነው ተብሏል።

ለዚህም መፍትሄ ለመስጠት ሰዎችን ከእንስሳቱ መኖሪያ ፓርክ ርቀው እንዲኖሩ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አቶ ኩመራ ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ትኩስ ዜናዎችን፣ ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *