የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ 27 ሚሊየን ዜጎች ሜዳ ላይ እንደሚጸዳዱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የዓለም የመፀዳጃ ቤቶች ቀን በማስመልከት በአዲስ አበባ የተለያዩ የህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች፣አመራሮች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እየተወያዩ ነው።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ በውይይቱ ላይ እንዳሉት 27 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን አሁንም ሜዳ ላይ ይጸዳዳሉ።

በኢትዮጵያ ከሚከሰቱ ህመሞች 30 በመቶ የሚሆኑት ተላላፊ በሽታዎች መንስኤያቸው ከመጸዳጃ ቤትና ከአካባቢ ንጽህና ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል።

ዜጎች ጥንቃቄ ከማድረግ ይልቅ ሲታመሙ ብዙ ወጪ ያወጣሉ ተብሏል መንግስትም ይሄን ለማከም በርካታ ወጪዎችን ያወጣሉ ብለዋል ዶክተር ደረጀ።

ይህ በመሆኑ ምክንያት ተላላፊ በሽታዎች በመጨመሩ በየዓመቱ ከ13 ቢሊዮን በላይ ብር ለመድሃኒት ግዥ እና ለሌሎች ህክምና ወጪዎች እንደሚወጣም ዶክተር ደረጀ ገልጸዋል።

በሜዳ ላይ የሚጸዳዱ ዜጎችን ቁጥር ለመቀነስ ጤና ጥበቃ ሚኒስሬር በሚቀጥሉት 10 አመታት ኢትዮጵያን ከውጭ መጸዳዳት ነጻ ሀገር ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዋል።

አሁንም ሜዳ ላይ የመጸዳዳት ልማድ ያለው የህብረተሰብ ክፍል እንዳለ የተነገረ ሲሆን 27 ሚሊየን ዜጎችም ሜዳ ላይ ይጸዳዳሉ ተብሏል።

ከ10 አመት በፊት መጸዳጃ ቤት የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር 40 በመቶ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን 70 በመቶ መድረሱም ተገልጿል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *