ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን ለፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ 14 መኪኖችን ድጋፍ አደረገ፡፡

ጠቅላይ አቃቤ ህግ የፍትህ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የመኪና ድጋፍ ከኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን ድጋፍ እንደተደረገለት አስታውቋል።

በሀገሪቱ የሙስና ወንጀሎች፣ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ላይ የተሰማሩ ቡድኖች እና ግለሰቦች የሚያደርሱትን ወንጀል ለመከላከል የሚያስችል ነው ድጋፉ፡፡

ተቋሙ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር በዜጎች ህይወት እና ንብረት ላይ ተደጋጋሚ ጉዳት እያደረሱ የሚገኙ ህግ ተላላፊዎች ላይ አስፈላጊው እርምጃ ለመውሰድ የተሸከርካሪ እጥረት እንደነበረ ነው የተገለጸው፡፡

ህግ ለማስከበር በሚደረግ ጥረት ውስጥ ማነቆ ከነበሩ አበይት ጉዳዮች መካከል አንዱ የምርመራ ቡድኑን እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ያለ ችግር ተንቀሳቅሰው የሚሰሩበት ተሽከርካሪ በበቂ አለመኖሩ የስራ እንቅፋት መሆኑን ነው የተነገረው፡፡

ይህንን ከፍተኛ የሆነ የተሽከርካሪ እጥረት ለመፍታት በኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን በተገኘ ድጋፍ 12 ፒካፕ እና ሁለት ሀርድ ቶፕ በድምሩ 14 ተሽከርካሪዎች ተገዝተው ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጋቸውን ተቋሙ ገልጿል፡፡

ተሽከርካሪዎች ተቋሙ በቀጣይ የህግ ማስከበር ሚናውን በተሻለ እንዲወጣ በከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋልም ሲል ነው ያስታወቀው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሕዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *