ሀዋሳ ከተማ የራሷ መገለጫ የሆነ ምልክትን (Logo) አጸደቀች።

የሀዋሳ ከተማ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት አለም አቀፉን መስፈርት ታሳቢ በማድረግ ከተማዋ የራሷን ምልክት ይፋ አድርጋለች ብለዋል።

አዲሱ ምልክት የሀዋሳን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ተፈጥሯዊ እና የሰው ሰራሽ ሀብቶቿን ታሳቢ ያደረገ ነውም ብለዋል።

ምልክቱ በሚቀጥሉት ጊዜያት በሁሉም የአስተዳደሩ እርከኖች ማናቸውም ከተማዋን በሚመለከቱ ተግባራት ተፈጻሚ ይሆናል ስለመባሉ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *