በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ሸዋ ችሎት የቀረቡት አቶ ልደቱ አያሌው አቃቢ ህግ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ችሎቱ በአቃቢ ህቅ የተጠቀሱት አንቀፅ 238 እና አንቀፅ 256 ግልፅነት የሚጎላቸው ናቸው በሚል አቃቢ ህግ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ በሚል ነው ቀጠሮ የሰጠው፡፡

ኦሮሚያ ጠቅላላ ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውንም ክሱ ግልፅ ባልሆነበት እና ባልተሻሻለበት ሁኔታ ብይን መስጠት አንችልም በሚል የዋስትናውን ጥያቄ ውድቅ አድርጉታል ብለውናል የፖርቲው ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ።

አቶ ልደቱ ችሎቱ ላይ ከታሰሩ አራት ወር እንደሆናቸው አስረድተው የዘገየ ፍትህ እንደተነፈገ ይቆጠራል ብለዋል፡፡

የታሰርኩት በሴራ በመሆኑ የተከበረው ፍርድ ቤት የዚህ እኩይ ስራ ተባባሪ መሆን የለበትም ማለታቸውን አቶ አዳነ ነግረውናል፡፡

ለችሎቱ እና ለለበሳችሁት ካባ ክብር ስትሉ ተገቢውን ፍርድ ትሰጣላችሁ ብዬ እጠብቃለሁ ማለታቸውንም አቶ አዳነ ይናገራሉ፡፡

ጠቅላላ ፍርድ ቤቱ የተሻሻለውን ክስ ለመስማት ለህዳር 24/2013 ዓ/ም ከቀኑ 8 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *