የካፍ ፕሬዝዳንት በፊፋ የአምስት ዓመት ዕገዳ ተጣለባቸው።

የፊፋ ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ የአምስት ዓመት ዕገዳ የተጣለባቸው በርካታ የስነምግባር ደንቦችን መጣሳቸው ተነግሮ ነው፡፡

የ60 ዓመቱ የፊፋ ምክትል ፕሬዝዳንት የታማኘነትን መርህ መጣሳቸውን ቢቢ9ሲ ዘግቧል፡፡

‹‹ስጦታዎችን›› ይሰጣሉ ፣ ይቀበላሉም ተብሏል፡፡ ስልጣናቸውን ያለ አግባብ ይጠቀማሉ እንደዚሁም ለሌላ ዓላማ ተያዘ ገንዘብ አለአግባብ ይጠቀማሉ በሚል ተወንጅለዋል፡፡

‹‹ ከ2017 እስከ 2019 በአህመድ ላይ ከካፍ ጋር የተገናኙ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ምርመራ ተደርጓል፡፡ በተለይም ካፍ ከስፖርት ቁሳቁስ አቅራቢ ካምፓኒ ታክቲካል ስቲል ጋር የነበረውን ግንኙነት የመሩበት መንገድ ተዳስሷል›› በማለት ፊፋ በመግለጫው አስፍሯል፡፡

አህመድ በተጨማሪም 200 ሺ ዶላር ቅጣት የተጣለባቸው ሲሆን ሰውየው ከዚህ ቀደምም የቀረቡባቸውን ውንጀላዎች ማስተባበላቸው ይታወቃል፡፡

ማዳጋስካራዊው በስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ይግባኝ መጠየቅ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

በአቤል ጀቤሳ
ሕዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *