በኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 929 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ማጣታቸው ተገለጸ።

ከዚህ በተጨማሪም 2 ሺህ 512 ሰዎች ደግሞ ለከባድ የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ በዚሁ የ2013ቱ ሩብ አመት በትራፊክ አደረገ 929 መሞታቸውንና 2 ሺህ 512 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጂሬኛ ሂርጳ ገልጸዋል።

ከተጎጂዎቹ ብዙወቹ ደግሞ መንገደኞች ናቸው ብለዋል ዳይሬክተሩ።

በሀገራችን የመንገድ ትራፊክ አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል ኢንጂነር ጂሬኛ።
በመሆኑም አሽከርካሪዎች መብራትን ጠብቆ ማሽከርከር፣ ከበቶን በአግባቡ በመጠቀም፣ የትራፊክ መመሪያዎችንና ትእዛዝን ማክበርና መተግበር እንዲሁም ሞባይልን ጨምሮ ትኩረትን ከሚነሱ ነገሮች ተቆጥበው ማሽከርከር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

እግረኞችም በዜብራ ማቋረጫዎች በማቋረጥና መኪና ማለፍ አለማለፉን ጠብቆ ግራናቀኝ በማየት በጥንቃቄ ማለፍ አለባቸው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በተያያዘ መረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ እንደ ፈረንጆቹ 2020 ዓ.ም በትራፊክ አደጋ ምክንያት 1 ነጥብ 35 ሚሊዮን ሰዎች ህይዎታቸውን ማጣታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት የዘንድሮው ዓመታዊ ሪፖርት ያሳያል።

50 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ለከባድ የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን የዚሁ ተቋም ሪፖርት ጠቁሟል።

በዚህም በአለማችን በትራፊክ ግጭት ምክንያት በየ24 ሴኮንዱ የአንድ ሰው ህይወት ያልፋል ሲል ሪፖርቱ አክሏል።

ከተማችን አዲስ አበባም ከዚሁ የትራፊክ አደጋ ነፃ አልወጣችም። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ እንደሚያሳየው በ2011 ዓ.ም 458 ሰዎች፣ በ2012 ዓ.ም ደግሞ 450 ሰዎች በትራፊክ ግጭት ምክንያት መሞታቸውን ገልጿል።

በተጨማሪም በ2011 ዓ.ም 1 ሺህ 926 ሰዎችች እንዲሁም በ2012 ዓ.ም 1 ሺህ 673 ሰዎች ደግሞ ከባድ የሆነ የአካል ጉዳት ድረሶባቸዋል ሲል መረጃ አውጥቷል።

በጅብሪል ሙሃመድ
ሕዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.