በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ችግር ውስጥ ለገቡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች 250 ሺህ ብር መስጠቱን የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር አስታወቀ።

የኮሮና ቫይረስ ካሳለፍነው የካቲት ወር አንስቶ በመከሰቱ ምክንያት የበርካታ ዜጎችን ህይወት አመሰቃቅሏል።

በኢትዮጵያም ቫይረሱ ከተከሰተበት መጋቢት ወር 2012 ዓ.ም አንስቶ በተለይም ህይወታቸውን ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው የሚደጉሙ ዜጎች ለከፋ ችግር ዳርጓቸዋል።

ሲኒማ ቤቶች እና ትያትር ቤቶች በመዘጋታቸው ምክንያት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ለችግር አጋልጧል።

የባህልና ርሪዝም ሚንስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በቫይረሱ ምክንያት ለከፋ ችግር ለተጋለጡ 23 የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች 250 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።

ሚንስቴሩ የተጠቀሰውን ገንዘብ ከተለያዩ አካላት በማሰባሰብ በሀገር ደረጃ 23 ጉዳት ለደረሰባው ለባህልና ጥበባት ሙያተኞች (አርቲስቶች) ለእያንዳንዳቸው 1አሥር ሺህ ብር በመሥጠት መርዳት ተችሏል ብሏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.