በኮንሶ ዞን እና በአሊ ልዩ ወረዳ እንዲሁም በደራሼ ልዩ ወረዳ እና በኮንሶ የተከሰተው ግጭት ሙሉ ለሙሉ መብረዱን የደቡብ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የደቡብ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ለኤትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት በእነዚህ አከባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ብሔረሰብ ተኩር ለማስመሰል የተደረገውን ጥረት ከሽፏል፡፡

በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ህግ የማስከበር ስራ ለማጠናከር በአከባቢው ላይ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት መልቀቁን ተከትሉ አጋጣሚውን ለመጠቀም ከህውሀት እንዲሁም ከኦነግ ሸኔ ጋር ሲል ያላቸው እና ለዘመናት ሲጠነስሱት የነበረው ሴራ ያላቸው ግለሰቡች አላማቸውን ለማሳካት ግጭቱን እንደቀሰቀሱት ይናገራሉ አቶ አለማየሁ፡፡

በደራሼ ልዩ ወረዳ እና በኮንሶ መካከል ግጭቱ የብሔረሰብ ለማስመሰል ኮታ ገጠም የሆኑ አርሶ አደሮች እርስ በእርስ እንዲጋጩ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

በተመሳሳይ በኮንሶ እና በጉርጂ-አማሮ አማካኝ አከባቢ የልዩ ወረዳ ጥያቄን እናስመልስላችኋለን በሚል በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር ደርስንበታል ብለውናል፡፡

በዚህ ሰበብም ህይወት ጠፍቷል፤በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ንብረት ወድሟል፤በርካቱችም ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡

በአጠቃላይ የደረሰውን ጉዳት እና በዚህ ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ የሆኑትን ሰዎች ፖሊስ በቅርቡ ምርመራውን እንዳጠናቀቀ ይፋ እንደርጋለን አሁን ግን መናገር አልችልም ብለውናል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *