አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የእሳት ቃጠሎ ህክምናና የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና መስጠት ጀመረ።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የእሳት ቃጠሎ ህክምናና የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል።

በዚህም ሆስፒታሉ በኢትዮጵያ ከየካቲት ሆስፒታል ቀጥሎ ሁለተኛው የእሳት ቃጠሎ ህክምና ማዕከል ነው ብለዋል።የስዊድን የህክምና ቡድን 15 ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ለማዕከሉ እንዳደረጉላቸውም አቶ ተመስገን ነግረውናል።

የስዊድን የህክምና ቡድን የጤና ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ስምምነት እንዳደረጉም ሰምተናል።የእሳት ቃጠሎ ህክምናና የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ክፍሉ አሁን ላይ በተሟላ መልኩ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛልም ተብሏል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *