ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ድርጅት 858 የሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን እንዳልተቀበለ አስታወቀ።

የትግራይ ቴሌቪዥን በትናንት ምሽት ዘገባው ባሰራጨው መረጃ በትግራይ መንግስት ስር ያሉ 858 የሰሜን ዕዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ለዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስረክበናል ብሎ ነበር።

በርክክቡ ወቅትም የቀይ መስቀል አባላት በአካል ተገኝተው ነበርም ሲል ነው ቴሌቪዥን ጣቢያው የገለፀው።ይሁንና ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ተቋም ግን 858 የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን እንዳልተቀበለ በድረገፁ አሳውቋል።

ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት የተጎዱ ዜጎችን ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል።ድርጅቱ ከሁለቱም ወገኖች የተጎዱ ዜጎችን በ11 አንቡላንሶችን በማሰማራት ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጿል።

በጦርነቱ የተጠፋፉ ቤተሰቦችንም የማገናኘት ስራ በመስራት ላይ ሲሆን አሁንም ቤተሰብ የጠፋባችሁ ዜጎች በስልክ ቁጥር 0943122207 ወይም በ0115527110 ደውላችሁ ብታስመዘገቡ ልንረዳችሁ እንችላለን ብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም
የኢትዮጵያውያን
ሕዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *