ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የኤሎክትሪክ ኃይል ተቋርጧል፡፡

የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት የኮሚኒኬሽን ሀላፊ አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩትም ከቀኑ 7:00 አካባቢ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ነው የኃይል አቅርቦቱ የተቋጠው ብለውናል፡፡

እርሳቸውም በመላ ሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ገልጸዋል፡፡

በቴክኒክ ችግር የተቋረጠውን ኃይል ለመመለስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የቴክኒክ ክፍል ርብርብ በማድረግ ላይ እንደሚገኑም ነግረውናል።

በቀጣይ አንድ ሰዓት ውስጥ ደረጃ በደረጃ ኃይል የማገናኘት ስራዎች የሚሰሩ መሆኑን መስራያቤቱ አስታውቋል፡፡

እንደ ሞገስ ሀሳብ ከሆነ የቴክኒክ ብለሽት መሆኑን ለማረጋገጥ ችግሩ መታወቅ አለበት አሁን ላይ የት አካባቢ ላይ ችግሩ እንደተከሰተ ለማወቅ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሕዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.