የአሜሪካ ተመራጩ ፕሬዘዳንት አንቶኒ ብሊንከን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አድርገው ሾሙ።

በ44ኛው የአሜሪካው ፕሬዘዳንት በሆኑት ባራክ ኦባማ ስልጣን ዘመን ምክትል ፕሬዘዳንት ሆነው ያገለገሉት ጆ ባይደን እጩ ካቢኖያቸውን አቅርበዋል።

በአሜሪካ የስልጣን ደረጃ ከፕሬዘዳንቱ በመቀጠል ቁልፉ ቦታ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርነት ቦታ ነው።

ተመራጩ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን አንቶኒ ብሊንከንን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አድርገዋል።

በባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን ሂላሪ ክሊንተንን በመተካት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት ጆን ኬሪ የአየር ንብረት ባለስልጣን አድርገዋቸዋል።

የኦባማ የጸጥታ አማካሪ የነበሩት ሱዛን ራይስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ተደርገው ይሾማሉ የሚል ሹክሹክታ በሰፊው ይሰማ የነበር ቢሆንም በባይደን ካቢኔ ውስጥ ሳይካተቱ ቀርተዋል።

አንጋፋዋ ጥቁሯ ዲፕሎማት ሊንዳ ቶማስ ደግሞ በመንግስታቱ ድርጅት የአሜሪካ ተጠሪ ሆነው እንደሚሾሙ ባይደን አስቷውቀዋል።

የሊንዳ ሹመት በጥቁር አሜሪካዊያን ታሪክ አዲስ ክስተት መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ጃክ ሱቪሊያን ደግሞ የአሜሪካ ደህነት አማካሪ እንደሚሆኑ ከሁለት ወር በኋላ ወደ ነጩ ቤተመንግስት የሚገቡት ተመራጩ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ገልጸዋል።

በሳሙኤል አባተ
ሕዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *