በአዲስ አበባ በሁለት ሳምንት ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ ከረጢት ደም መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡

የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ10ሺህ ቀረጢት በላይ ደም መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የብሄራዊ ደም ባንክ የደንበኞች አገልግሎት ሀላፊ ዶ/ር ተመስገን አበጀ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የመከላከያ ሀይል በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የደም ሰጪዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል፡፡

በመሆኑም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የደም ማሰባሰቡ ሂደት በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ግጭቱ ባለባቸው አካባቢዎችም እስካሁን ድረስ ምንም የደም እጥረት አልተከሰተም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መከላከያ ሰራዊት የራሱ የደም ባንክ ስላለው ግጭቱ ባለባቸው አካባቢዎች በመከላከያ በኩል እንዲደርሳቸው እያደረግን ነው ብለዋል፡፡

በአማራ ክልል በጎንደር በባህር ዳር በደብረ ማርቆስ በደሴ በወልዲያ የደም ማሰባሰቡ በጥሩ ሁኔታ እየተሰበሰበ እንደሆነም ነው ዶ/ር ተመስገን የተናገሩት፡፡

የህዝቡ ደም የመለገስ ባህል እንዳለ ሆኖ ባሁኑ ሰአት ደግሞ ይበልጥ አጠናክሮ በከፍተኛ ፍላጎት ደም እየለገሰ ይገኛል ብለዋል ሀላፊው፡፡

በመሆኑም ህዝቡ ደም የመለገስ ባህሉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሕዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *