አክሽን ኤድ ኢትዮጵያ ለሜቄዶንያ ከ885 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ቁሳቁስ ለገሰ።

አክሽን ኤድ ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት እናቶችና ህፃናት ላይ በሚከሰቱ ማንኛውም ችግሮች እርዳታ ያደርጋል፡፡

አክሽን ኤድ ኢትዮጵያ ለሀገራችን ኢትዮጵያም ኮሮናን ጨምሮ ሌሎች ወረርሽኞች ሲያጋጥሙ ቀድሞ ለህብረተሰቡ በመድረስ ግንባር ቀደም እንደሆነ ስራቸው ይመሰክራል ብሏል ሜቄዶንያ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ።

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ምንም እርዳታ ወደ ማዕከሉ እየመጣ እንዳልሆነ የተገነዘበው አክሽን ኤድ ኢትዮጵያ ለመቄዶንያ የ200 ኩንታል ጤፍ ፣ 800 ሊትር የምግብ ዘይት፣ 504 ሊትር ፈሳሽ ሳሙና፣ 150 ሊትር ሳኒታይዘር፣ 270 ፍሬ የኣዋቂ ዳይፐር፣ 30 ፍሬ ማስክና ሌሎችን በአጠቃላይ በድምሩ 885 ሺህ 855 ብር የሚያወጣ ቁሳቁስ እና አስቤዛ ለመቄዶንያ እርዳታ አድርገዋል ተብሏል፡፡

በበጅብሪል ሙሃመድ
ሕዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.