የተዘረፉ የኢትዮጵያ ቅርሶችን የሚያስመልስ የቅርስ አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ሊቋቋም ነው።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ እንደገና ደሳለኝ በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የተዘረፉ ቅርሶችን የሚያስመልስ የቅርስ አስመላሽ ብሄራዊ ኮሚቴ ሊያቋቁም መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ቅርስ በተለያዩ ጦርነቶች እንዲሁም በዝርፊያ በተለያዩ አፍሪካን ጨምሮ በአለም ሀገራት ይገኛሉ።

እነዚህን ኢትዮጵያዊ የሆኑ ቅርሶችን ቅርሶቹ ከሚገኙባቸው አገራት ጋር በመደራደር የሚያስመልስ ኮሚቴ ዛሬ በአዲስ አበባ እንደሚቋቋም ተገልጿል።

የብሄራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴው ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎች ያሉት መሆኑንም ሰምተናል።

የህግ ባለሙያዎች የታሪክ ምሁራን አርኪዎሎጂስቶች የኪነጥበብ ሰዎች እና ሌሎችንም አካቷል።

ኮሚቴው በዛሬው ዕለት ተቋቁሞ የራሱን ሊቀመንበርና የየደረጃ ሀላፊዎችን ይሾማል ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *