ራስ ደስታ ሆስፒታል የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር የህክምና አገልግሎት በነጻ መስጠት ጀመረ፡፡

ሆስፒታሉ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር የህክምና እና የምርምራ አግልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ይትባረክ ሀይሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት እድሜያቸው ከ25 እስከ 49 ለሆኑ እናቶች በነጻ የቅድመ ካንሰር ምርመራ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የነጻ ህክምና እና ምርመራ አገልግሎቱን የሚፈልጉ እናቶች ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ቀን ያለ ምንም ክፍያ መስተናገድ ይችላሉም ብለዋል ዶ/ር ይትባረክ፡፡

የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ በሴቶች ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በዓለም በየዓመቱ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ በአዲስ መልክ የሚያዙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡

ከሚሞቱት መካከልም 90 በመቶዎቹ የሚገኙት እንደ ኢትዮጵያ አይነት በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ነው፡፡

ከአጠቃላይ የህዝባችን ቁጥር እድሜያቸው ከ30-49 የሚሆኑ 10 ሚሊዮን ሴቶቸ ለማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ የታለሙ ናቸው፡፡

በሃገራችን በየዓመቱ ወደ 7 ሺህ የሚሆኑ ሴቶች በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ ይያዛሉ፡፡

የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በሽታን ለመከላከል ክትባት አይነተኛና አዋጭ መፍትሄ ነው፡፡

እንደዚሁም የማህጸን በር ካንሰር ጫፍ ቅድመ ምርመራ በማድረግ መከላከል እንደሚቻል ባለሞያዎች ይመከራሉ፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሕዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *