አዋሽ ባንክ 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር አመታዊ ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ ።

አዋሽ ባንክ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 25ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።

ባንኩ በ2019/ 2020 አጠቃላይ የትርፍ መጠን የስንምት በመቶ ዕድገት በማሳየት 3.6 ቢሊየን አመታዊ ትርፍ ማግኘቱ ገልጿል ።

ባንኩ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 57 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ብድር ማበደሩንም አስታውቋል።

ባንኩ እንዳስታወቀው በ2019/ 2020 በጀት ዓመት የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 74 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጿል።

ይህም ከዚህ በፊት ከነበረው የ19 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተገልጿል።

በበጀት አመቱ ማጠቃለያ የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠን 19.7 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ 89.3 ቢሊየን ብር መድረሱንም ተነግሯል ።

በዳንኤል መላኩ
ሕዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.