የኢራን ቦምብ አባት በመባል የሚታወቁት ኢራናዊው ፋክህሪ ዛዴህ በቴህራን ተገደሉ።

ኢራን የኑክሌር ሳይንስ ተመራማሪዋ በእስራኤል እንደተገደለባት ገልጻለች።

ተመራማሪው ፋክህሪ ዛዴህ ትላንት በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን አቅራቢያ በመኪና በመጓዝ ላይ እያሉ ነበር በጥይት ተመተው ሂወታቸው ያለፈው ፡፡

የኢራን ከፍተኛ የኑክሌር ሳይንቲስት የሆኑት ሙህሰን ፋክህሪ ዛዴህ በረቀቀ መንገድ መገደላቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሀኒ በዚህ ግድያ እስራኤልን ከሰዋል፡፡

አንጋፋው የኢራን የኒውክለር ተመራማሪ ሙህሰን ፋክህሪ ዛዴህ የገደለችው እስራኤል ነች ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ሀገሪቷን እንደወቀሱ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ይህ ሰይጣናዊ ድርጊት የፈጸመችው እስራኤል መሆኗን ለማረጋገጥ ምንም አይነት ማስረጃ አያስፈልግም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ ለሀገራቸው ሚዲያ ባስተላለፉት መልእክት፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃመድ ጃቫድ ዛሪፍ በበኩላቸው ግድያውን የሃገር ሽብር ሲሉ አውግዘው ከግድያው ጀርባ አሜሪካ እና እስራኤል መኖራቸውንም አውስተዋል፡፡

ፋክህሪ ዛዴህ የኢራን የቦምብ ፈብራኪ አባት በመባል ይታወቅ ነበር ፡፡

ምንም እንኳን ኢራን የኑክሌር መርሃ ግብሯን ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ እንደሆነ አጥብቃ ብትከራከርም ፡፡

ሟቹ ተመራማሪ የእስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን ወታደራዊ ሀይል እና የኑክሌር መርሃ ግብር ኃላፊ ነበሩ።

እስራኤል በኢራን በኩል ክስ ይቅረብባት እንጂ በጉዳዩ ዙርያ ያለችው ነገር የለም፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሕዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.