ማደሪያ ያጣች እንስትን እኔ ጋር ታድሪያለሽ በሚል በማታለል ወደ ቤቱ በማስገባት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ18 ዓመት እስራት ተቀጣ

ወንጀሉ የተፈጸመባት እንስት ህይወቷ ማለፉም ተገልጿል።

ተከሳሽ አብዱ መሐመድ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ክልል ልዩ ቦታው አሜሪካን ግቢ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ለጊዜው ማንነቷ ያልታወቀ ሟች ማደሪያ ችግሯት ከኔ ጋር ታድሪያለሽ በማለት ይዟት ከሄደ በኃላ ካልተያዙ አምስት የወንጀል ተካፋዮች ጋር በመሆን ሀይል በመጠቀም አስገድደው የመድፈር ወንጀል ሲፈጸሙባት በደረሰባት አካላዊ ጉዳት ምክንያት ህይወቷ ያለፈ በመሆኑ ተከሳሽ በፈጸመው የወንጀል ድርጊት ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡን የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡

ዐቃቤ ሕግም በክሱ መሰረት ገላጭ የሆኑ የሰው እና የሰነድ ማሰረጃዎችን አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

የክሱ ዝርዝር በችሎት የተነበበለት ተከሳሽም በወንጀል ድርጊቱን መቃወሚያ እንደሌለው ገልጾ ክሱን ክዶ ተከራክሯል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር በማድመጥ፣ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን ከመረመር በኃላ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ተብሏል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎትም ክስና ማስረጃውን ከሕግ ጋር አገናዝቦ ተከሳሽን በፈፀመው ወንጀል በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የፈደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሕዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.